Welcome To Enor Woreda
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ መልዕክት
“ በቅድሚያ እንኳን ወደ ጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ድህረ ገጽ ላይ በሰላም ተቀላቀሉ /መጡ
አለም በቴክኖሎጂ ምክንያት ወደ አንድ መንደር ላይ በተሰባሰበችበት ወቅት ላይ ከመሆናች ጋር ተያይዞ ይህ ድህረ ገጽ ከወረዳችንም ባሻገር ለብዙኋኑ ጊዜ ጉልበት ገንዘብ የሚቆጥብ መሆኑ ግልጽ ነውና ለተገቢና ለተገቢ አላማ ብቻ እንድንጠቀመው ቅድሚያ አደራ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ወረዳችን እኖር የብዙ ጸጋ ባለቤት የሆነች ለኑሮ ተስማሚ ህዝቦች ተዋደውና ተቻችለው የሚኖሩበት ባለ ብዙ ታሪክ ወረዳ ስትሆን የዚህም መገለጫ ደጋ ወይናደጋ ቆላ ወይም 3ቱ የአየር ንብረት የያዘች ሰፊ የመሬትና የኢንቨስትመንት አማራጭ ያላት መስኖ በበልግ በመኸር የሚለማበት የብዙ ተፈጥሮ ጸጋ ባለቤት ናት ላለፍናቸው አመታትም ሆነ አሁንም የወረዳው ህዝብ ከራሱ አልፎ ሀገራዊ ተልእኮዎች ላይ የራሱ ድርሻ ሲወጣ መጥቶዋል እየተወጣ ይገኛል የቀጠለ ተግባር ነው፡፡ወረዳችን አንዱ ተመራጭ የሚያደርጋት ለማእከላዊ ኢትዮጲያ መቀመጫዎችም ሆነ ለኢትዮጲያ ዋና ከተማ በቅርብ የምትገኝ ከወረዳችን ወደ ዋና ከተማ በየቀኑ ምርት የሚመላለስበት ከአዲስ አበባ ወደ ወረዳችን በተመሳሳይ ሁኔታ ግብዓት የሚቀርብበት ነው፡፡ሆኖም ግን ወረዳችን ካሉት እምቅ አቅም አንጻር ከዚህ በላይ በሁሉም ዘርፍ መልማት ትፈልጋለች ለዚህ ደግሞ ማህበረሰብ ተወላጁ ባለሀብቱ እንዲሁም ባለ ድርሻዎች ከወረዳው መንግስት ጎን በመቆም እጅ ለእጅ ተያይዞ ማልማት የሁላችን ሀላፊነት ሊሆን ይገባል እላለሁ ፡፡በመጨረሻም ያሉን እድሎችና ሀብቶች በፍትሀዊነት በመጠቀም የጎደሉንን በጋራ ሁላችንም ተግባብተን በመሙላት የወረዳችንና የሀገራችን ሁለተናዊ ብልጽግና ወደ ፊት እናራምዳለን ፡፡ "
ስለ እኖር ወረዳ
የአስተዳደር ታሪክ











እኖር ወረዳ ከ 1983ዓ.ም ጀምሮ ያስተዳደሩት መሪዎች
እኖር ወረዳ በጉራጌ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ ሲሆን የሚያዋስናቸው በደቡብ ከእኖር ኤነር ወረዳ፣በደቡብ ምዕራብ ከየም ዞን፣በምዕራብ በኦሮሚያ ክልል፣በሰሜን በቸሃ፣በምስራቅ በጌታ እና በደቡብ ምስራቅ በኩል ይዋሰናል የእኖር ወረዳ የአስተዳደር ማእከል ጉንችሬ ነው።
የእኖር ወረዳ ስያሜ
የእነሞርና ኤነር ወረዳ ምክር ቤት ግንቦት 2 / 2014 ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ ዙር 8ኛ ዓመት 30ኛ መደበኛ ጉባኤ ወረዳው ቀደም ብሎ…
Direction of Enor Woreda
Map & Location Enor Woreda , Gurage Zone
Enor Woreda According to the data obtained from GIS, the total area of Enor Woreda is estimated to be 113,467 hectare. Of this, 15767 hectare is for annual crops, 57364 hectare is occupied by permanent crops, 10,882 hectare can be cultivated in the future, 7500 hectare is for grazing land, 1307 hectare is natural forest, 7388 hectare is artificial forested land, 1636 hectare is damaged land. Land covered by water is 2120 hectare, land covered by residential premises is 5000 hectare, land owned by government institutions is 2139 hectare, land covered by other miscellaneous holdings is 2364 hectare. The structure of the district is composed of 40 rural kebeles and 3 urban kebeles.
The topography of the district is mostly plain and the rest of the area is covered with natural and man-made forests and is mountainous and steep. The climate of the district is 57.22% altitude above sea level (1500 – 2300m), lowland 26.25% altitude above sea level (801 – 1500m) and 16.23% plateau and altitude is estimated to be above sea level (2300 – 3400m). The annual temperature of the district is estimated to be a maximum of 25°C and a minimum of 13°C. Maximum annual rainfall is 1400mm and minimum is 801mm. In the district rivers, Nueharam, Ensharam, Gogare, Winqe, Nakam etc. are our natural blessings.
About Developer
mukeremsano@gmail.com
+251970847834